Skip to content
Join us on Telegram
Explore jobs
Pricing
Log in
Get started
→
የግል ረዳት (Personal Assistant) Job in Addis Ababa | AradaJobs
Explore jobs
Pricing
Log in
Get started
→
Back to Jobs
Job Details
የግል ረዳት (Personal Assistant)
A and M Engineering PLC
Full-time
Addis Ababa, Addis Ababa
About this role
የግል
ረዳት የስራ መግለጫ
የስራ አስፈፃሚውን ዕለታዊ የቀን መቁጠሪያ፣ ቀጠሮዎች፣ ስብሰባዎች እና መርሃ ግብሮች ማስተባበር እና መፈፀም።
የጉዞ ዝግጅቶችን ማስተባበር፤ በረራዎችን፣ ሆቴሎችን፣ መጓጓዣዎችን እና የጉዞ መርሃ ግብሮችን መከታተል እና ማቀናጀት።
ኢሜሎችን፣ የስልክ ጥሪዎችን እና ሌሎች ደብዳቤዎችን ተገቢውን ምላሽ መስጠትና መከታተል።
ሰነዶችን፣ ሪፖርቶችን፣ አቀራረቦችን፣ ፕረዘንቴሽን እና የስብሰባ ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት።
ስብሰባዎችን ቀጠሮዎችን፣ ኢግዚቪሽኖችን ማቀናጀትና ማስተባበር፤
የስብሰባ ቃለ-ጉባኤ ማስታወሻዎችን መያዝ፣ መዝገቦችን መጠበቅ እና የድርጊት ነጥቦች ከተሰጡ በኋላ የታዘዙ የሥራ አፈፃፀም መከታተል።
ሚስጥራዊ እና አስፈላጊ መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዝ ምስጢራዊነትን በመጠበቅ።
ኤሌክትሮኒክስ እና አካላዊ ፋይሎችንና ሰነዶችን በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ማደራጀት እና መያዝ።
የድርጅቱን እና ለግል ፍላጎቶች ጥናቶችን ማድረግ እና መረጃዎችን መሰብሰብ።
የወጪ እና የገቢ አካሄድ እና ደረሰኝ ተከታትሎ ከሂሳብ ክፍል ጋር ማስታረቅ።
በስራ አስፈፃሚው፣ በሰራተኞች፣ በደንበኞች፣ በአቅራቢዎች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ሥራ ግንኙነት ማስተባበር።
የግል እና የሥራ ነክ ጉዳዩች ከሚመለከተው አካል ጋር ጉዳዩን ለማየት ቀጠሮ ማስያዝ።
መልዕክቶችን ማድረስ እና እንዳስፈላጊነቱ የግል ጉዳዮች ላይ ዕርዳታ መስጠት።
የቀጠሮዎችን የመጨረሻ ቀናቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዩች ማስታወስ።
እንደአስፈላጊነቱ ፕሮጀክቶችን እና አስተዳደራዊ ስራዎችን መደገፍ።
የተደራጀ እና ምቹ የሆነ የስራ አካባቢን መፍጠር።
የስራ አስፈፃሚውን ፍላጎቶች አስቀድሞ መገመት እና የስራ መርሃ ግብር ወይም አስተዳደራዊ ችግሮችን በንቃት መፍታት።
ማይክሮሶፍት ኦፊስ፣ ጎግል ብቃት ያላት፣ የቀን መቁጠሪያ መተግበሪያዎችን እና ሌሎች መገልገያዎች መጠቀም።
በማንኛውም ጊዜ ሙያዊ ብቃትን፣ አስተማማኝነትን፣ ምስጢራዊነትን እና እጅግ በጣም ጥሩ ግንኙነትን መጠበቅ።
በ ISO እና ERP ሲስተሞች ላይ ቀልጣፋ መሆን።
ስራ አስፈፃሚዎችን በማንኛውም ጊዜ መደገፍ።
ቁልፍ ክህሎቶች
እጅግ በጣም ጥሩ ድርጅታዊ እና የጊዜ አያያዝ ክህሎት።
ጠንካራ የጽሁፍ እና የቃል ክህሎት በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ።
ለዝርዝር ነገሮች ትኩረት መስጠት።
ምስጢራዊነትን መጠበቅ።
ብዙ ስራዎችን በአንድ ጊዜ ማከናወን እና ቅድሚያ መሰጠት የሚገኝባቸውን መስጠት።
ችግር የመፍታት ክህሎቶች።
ሙያዊ የሰዎች ግንኙነት ክህሎት።
የቀን መቁጠሪያ እና የጉዞ አስተዳደር።
ማይክሮሶፍት ኦፊስ ጎግል እውቀት።
ራስን ችሎ የመስራት ችሎታ።
ተለዋዋጭነት እና ከሁኔታዎች ጋር መላመድ።
ጠንካራ ክትትል እና የስራ አስተዳደር ክህሎቶች።
Required Skills
Calendar Management
ERP Systems
Microsoft Office
Travel Coordination
How to apply
Send your CV and cover letter to dagimfikadu23@gmail.com. (Or apply as instructed in the job description.)
Apply externally
Job Overview
Job Type
Full-time
Location
Addis Ababa, Addis Ababa
Deadline
October 17, 2026
Vacancies
1
Education
Not Required
Experience
Entry
Gender
Both
Category
Secretarial & Office Management
Job Site
On-site
Posted
September 16, 2026