ሲኒየር ኦፕሬተር መካኒክ የሚከተሉት ኃላፊነቶች የሚኖሩት ይሆናል
- የምርት ማሽኖችን ደህንነት፣ የአሠራር ብቃትና የምርት ጥራት በተጠበቀ መልኩ ያስጀምራል፣ ያሠራል፣ ይቆጣጠራል፤ የማሽኖቹን የሥራ አፈጻጸምም በቀጣይነት ይከታተላል።
- የምርት ማሽኖች የታቀደላቸውን የምርት መጠን፣ ፍጥነት፣ ጥራትና የአሠራር ውጤታማነት እንዲያሟሉ ይከታተላል፤ ከታቀደው አፈጻጸም መዛባት ሲከሰት ምክንያቱን በመለየት ተገቢውን የአሠራር ማስተካከያ ያደርጋል።
- የምርት ጥራት ችግሮችን፣ የማሽን የአሠራር መዛባቶችንና ተደጋጋሚ የምርት ጉድለቶችን ይለያል፤ የችግሮቹን መንስኤ በመተንተን ተገቢውን የማስተካከያና የመከላከያ እርምጃ ይወስዳል፤ ከሥልጣኑ ወሰን በላይ የሆኑ ችግሮችን ለሚመለከተው ኃላፊ ያሳውቃል።
- የማይመጥኑ ምርቶችንና የጥራት ጉድለት ያላቸውን ግብዓቶች ከመደበኛው የምርት ሂደት እንዲለዩ ያደርጋል፤ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ተጨማሪ የጥራት ችግር እንዳይፈጠር ይከታተላል።
- 8 በየዕለቱ የማሽን እንክብካቤና ቀላል የጥገና ሥራዎችን፣ ማለትም Cleaning, Inspection, Lubricating and Tightening ያከናውናል፤ በሥልጣኑና በሙያዊ ብቃቱ ወሰን ውስጥ የሚገቡ መለዋወጫዎችን ይቀይራል፣ የማሽን ማስተካከያዎችንም ያከናውናል።
- የማሽኖችን የአሠራር ሁኔታ በየጊዜው በመመርመር የሚታዩ የመበላሸት ምልክቶችን፣ ያልተለመዱ ድምፆችን፣ ንዝረቶችን፣ የሙቀት መጨመርን፣ የዘይትና የአየር መፍሰስን እና ሌሎች የብልሽት ምልክቶችን ይለያል፤ ቀላል ጥገናዎችን ያከናውናል፤ ሌሎች ከበድ ያሉ ጥገናዎችን የጥገና ጥያቄ በማቅረብ እስከሚፈታ ድረስ ይከታተላል።
- የምርት ለውጥ ሲደረግ አስፈላጊው የማሽን ሞልድ፣ ዳይ፣ ፓንች፣ ቱል፣ ጂግና ሌሎች የምርት መለዋወጫ መሣሪያዎች በትክክለኛው መልኩ መዘጋጀታቸውን፣ መገጠማቸውንና መስራታቸውን ያረጋግጣል።
- ከምርት ለውጥ በኋላ የመጀመሪያ ምርት ሙከራ (First Piece/First Article Inspection) እንዲከናወን ያደርጋል፤ የምርት መስፈርቶች መሟላታቸውን ከጥራት ቁጥጥር ክፍል ጋር በመተባበር ያረጋግጣል።
- ለምርት ማሽኖች የሚያስፈልጉ ጥሬ ዕቃዎችን፣ ኬሚካሎችንና ሌሎች ግብዓቶችን በተገቢው መጠንና ጥራት እንዲዘጋጁና እንዲጠቀሙ ያስተባብራል፤ የግብዓት ብክነትን ይቆጣጠራል።
- የምርት ተረፈ ምርቶችን በዓይነታቸው እንዲለዩ፣ በተመደበላቸው ቦታ እንዲያዙና ከምርት ቦታ በአግባቡ እንዲወገዱ ይቆጣጠራል።
- በተመደበለት የምርት ክፍል ውስጥ ያሉ መካኒክ ኦፕሬተሮችና ጁኒየር መካኒክ ኦፕሬተሮች የዕለት ተዕለት የሥራ አፈጻጸምን ያስተባብራል፤ የሥራ ቅደም ተከተልን፣ የማሽን አጠቃቀምንና የቡድን ትብብርን ይከታተላል።
- በሥራ ቦታ የሚከሰቱ የምርት፣ የማሽን፣ የጥራትና የሥራ ደህንነት ችግሮችን በመለየት ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ይተባበራል፤ የተወሰዱ እርምጃዎችንም ይከታተላል።
- የምርትና የማሽን አሠራር መረጃዎችን፣ ማለትም የምርት መጠን፣ የጥራት አፈጻጸም፣ የማሽን የሥራ ሰዓት፣ የብልሽት ጊዜ፣ የግብዓት አጠቃቀም፣ የተረፈ ምርትና የመለዋወጫ አጠቃቀም መረጃዎችን በትክክል ይመዘግባል።
- የሽፍት ሪፖርትን ያዘጋጃል፤ የምርት አፈጻጸም፣ የጥራት ችግሮች፣ የማሽን ብልሽቶች፣ የምርት መቋረጥ ምክንያቶች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎችና ቀጣይ ክትትል የሚፈልጉ ጉዳዮችን በዝርዝር ያካትታል።
- የማሽን የሥራ አፈጻጸምን፣ የምርት ብክነትን፣ የማሽን ብልሽትንና የምርት መቋረጥን በመተንተን የችግሮቹን ዋና መንስኤዎች ይለያል፤ ለማሻሻያ የሚረዱ ሙያዊ ሀሳቦችን ለምርት ሱፐርቫይዘር ያቀርባል።
- በምርት ሂደት የሚታዩ የሥራ ብክነት፣ የጊዜ ብክነት፣ የማሽን የሥራ መቆራረጥና የጥራት ችግሮችን ለመቀነስ የKaizen እና የቀጣይ ማሻሻያ ሥራዎችን ያስተገብራል፤ ለማሻሻያ ሀሳቦችንም ያቀርባል።