ሲኒየር መካከኒክ የማምረቻ ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎች ተደጋጋሚና ውስብስብ ብልሽቶችን ይጠግናል በጥገና ወቅት የሚያስፈልጉ የጥገና መሳሪያዎች መፍቻዎች እንዲሟሉ ጥያቄ ያቀርባል፣ ሲፈቀድ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፣ የመከላከል ጥገና እንዲሁም መሳሪያዎችን ለብልሽት የሚዳርጉ ምክንያቶችን (Cause of failure) ጥገና በወቅቱ ጠብቆ ያካሂዳል፣ ያስተካክላል፣ ተፈጻሚነቱን ሪፖርት ያደርጋል፣ ለጥገና በወጣው ፕሮግራም መሠረት ሌሎች ቴክኒሽያኖችን (እንደ ብየዳና ኤሌክትሪሽያን) ጋር በመሆን ጥገናውን ማካሄድ፣መለዋወጫ ካስፈለገ መጠየቂያ ሞልቶ ያቀርባል፡፡ ሲፈቀድ አውጥቶ ጥገናውን ያካሂዳል፣ ሲጠናቀቅ ተገቢውን ሪፖርት ያደርጋል፣ እንዲሁም ለጥገና ስራ የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች መሳሪያዎች ሌሎችንም በአስፈላጊው ጊዜ እንዲቀርቡ ለቅርብ ኃላፊው ያሳውቃል በተፈላጊው ወቅት እንዲጠየቁ ያቀርባል፡፡